ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር/2/
እስመለአለም ምህረቱ እስመለአለም /4/
እናመስግናሽ የአምላክ እናት በዝማሬ /2/
የዓለም ቤዛ ነውና የማኅፀንሽ ፍሬ/4/
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከአንቺ ተወልዶ /2/
መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ /4/
በድንግልና የወለድሽው ክርስቶስ/2/
የድኩማኖች ብርታት ነው የሕሙማን ፈውስ/4/
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ/2/
በቸርነቱ ጠብቆ ከበደል አራቀን/4/
ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም ያዘከረ/2/
በመንግሥተ ሰማይ ይኖራል እንደተከበረ/4/
ብርሃነ መለኮት ያደረብሽ አዳራሽ/2/
ቅድስት ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ/4/
እመቤታችን እናታችን ማርያም/2/
የተማጸነሽ ይኖራ0ል ለዘለዓለም/4/
ድንልናሽ ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ
የጌታችን እናት ማርያም ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ
የጌታችን እናት ማርያም ንጽሕት ሆይ አንቺ ነሽ
በDec 09, 2024 ተጭኗል