እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

የዓለምን በደል

የዓለምን በደል

የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክት ትቶ
ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
የሰማዮች ሰማይ የማይችሉት ንጉሥ
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቀን ሲመሠርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
እንደምናነበው በወንጌል ተጽፎ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ
በርግብ ምሳሌነት ክንፉን አሰይፎ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
ባህር ስትጨነቅ ተራራው ሲጨፍር
ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር
አለም በዛሬው ቀን አየች ይህን ምስጢር

Download

በDec 09, 2024 ተጭኗል