እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ደጅ ጠናሁ
ደጅ ጠናሁ
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን /2/
♡ ♡
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟ ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት ያንቺ ደግነት
ባሪያሽን ሰወረኝ ካስጨናቂ ሞት
♡ ♡
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ ከፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ!
♡ ♡
ልቤ ባንቺ ፀና ከፍከፍም አለ
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል!
የሀያሉን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
♡ ♡
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ ከፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ!
♡ ♡
እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክራቸው ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸው
♡ ♡
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ ከፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
♡ ♡
በአውደ ምህረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችኝ ኪዳነ ምህረት
ሃሳብሽን ምንም የለ የሚመስለው
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነው
♡ ♡
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ ከፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
Download
በSep 21, 2024 ተጭኗል