እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ያዕቆብ ከቤርሳቤህ

ያዕቆብ ከቤርሳቤህ

ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሐይ ጠልቃ ነበር ከዛ እንደ ደረሰ
ከራሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ
ሕልምንም አለመ ታላቁን ራዕይ
መሰላል ተተክሎ ከምድር እስከ ሰማይ
ሲወጡ ሲወርዱ መላእክት በእርሷ ላይ
እግዚአብሔርም ቆሞ ከላይ ከጫፏ ላይ
የአባቶችህ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ
ይህንን ምድር ለእርስትህ እሰጥሃለሁኝ
ዘርህ እንደ አሸዋ በምድር ይዘራል
በአራቱም ማእዘን ሕዝብህም ይሆናል
አበው በምሳሌ እንደ ተናገሩት
ከምድር እስከ ሰማይ አምላክ የዘረጋው
በላይዋ ተቀምጦ በግልፅ የታየባት
የያዕቆብ መሰላል እመቤታችን ናት፤
ሰማይና ምድር የሚታረቁባት
ወልደ እጓለ እመሕያው የተወለደባት
መላእክት ከሰማይ በአንድ የዘመሩባት
ታላቋ መሰላል እመቤታችን ናት፤

Download

በSep 21, 2024 ተጭኗል