እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

መብልዕ

መብልዕ


መብልእ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ
ያስተፌስህ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ

ዘካርያስ አየ የገብርኤልን እውነት
በእርጅና ዘመንዋ ስትወልድ ኤልሳቤጥ
የልቦና መንገድ ከጥርጥር ጸድቶ
ዓለም ተደሰተ ልደትህን ሰምቶ

     ዮሐንስ መልአክ ለእግዚአብሔር ቅሩቡ
     ወርቀ ኪዳንከ ለነዳይ መዝገቡ

እንደምን ሰገደ በረታ ጉልበትህ
መለኮትን ጸንሳ ድንግል ስትጎበኝህ
ነፍሴ ታመስግንህ ይዘምር ልሳኔ
ውዳሴህን ላብዛ ላቅርብልህ ቅኔ

       ዮሐንስ ዘኮንከ ደመና ሰማይ ኮናኔ                  
      አዝንም መና አእምሮ ወሕብስተ ጥበብ መድኃኔ
    
የራጉኤል ትጋት የኢዮብ መታመን
መች ቻለ ሊዳስስ ነደ ነበልባሉን
በዮርዳኖስ ባህር አሳየህ መሷዋዕቱን
የአለምን ሐጢያት የሚያስወግደውን

       ዮሐንስ ጠቢብ ሐመረ ክርስቲያን ኃዳፊ
      ኢይትዔየረከ በዕበይ ዘሰማይ ሱራፊ

ከሴቶች ልጆች መሀል ዮሐንስ በለጠ
ናቡቴን መሠለው ለእውነት የተሰጠ
በመንፈስ ተጉዘህ  በኤልያስ ኃይል
ሳትፈራ መሠከርክ የእውነትን ቃል
  
         ዮሐንስ አንተ ጽልመተ አበሳ ሰዳዲ
         በአየረ ሰማይ ይጸርህ ቃልከ ዐዋዲ

መስክሪ ሄሮድያዳ የዮሐንስ ነገሩን
ታምኖ ቢሞት እንኳ በክንፍ መብረሩን
ምንኛ ታላቅ ነው ዮሐንስ ተጋድሎህ
ፈጥነህ ትደርሳለህ ዛሬም ለሚጠሩህ

ዮሐንስ ልብው መዝገበ ጥበብ ወአእምሮ
ፍፁመ መነንከ አብያተ ዘውቅሮ

ነቢየ ልዑል ፣ ሰማዕት ወ ጻድቅ ካህን ሐዋርያ
መምህር ወ መገስጽ ባህታዊ ድንግል መጥምቀ መለኮት
ርዕሰ አውደ ዓመት ጸያሔ ፍኖት
#አርኩ_ለመርዓዊ_ዮሐንስ_መጥምቅ(3)

Download

በSep 22, 2024 ተጭኗል