እንኳን ደህና መጡ
ግባ
አምላክ ለኛ ብሎ
አምላክ ለኛ ብሎ
አምላክ ለኛ ብሎ ቃልኪዳን የሰጣት/2/
የሐጥአን አማላጅ ድንግል ማርያም ናት/4/
እንደ አማለድሽው በላኤ ሰብዕን /2/
እኛንም እባክሽ አደራ አማልጅን/4/
ምህረት እንድናገኝ ከሐጥያታችን/2/
አማላጅ ሁኝልን እመቤታችን/4/
ከአንቺ በተገኘ የመልካሙ ፍሬ /2/
አለም ተቀድሷል ነጻ ወጥቷል ዛሬ /4/
ስምሽ ግርማ ያለው ኪዳነ ምህረት/2/
የሰዎች አማላጅ የጌታዬ እናት/4/
ካህናተ በከበሮ ሲያመሰግኑሽ/2/
እኛም በእልልታ እንዘምርልሽ/4/
Download
በSep 22, 2024 ተጭኗል