እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ቃና ዘገሊላ
ቃና ዘገሊላ
ቃና ዘገሊላ /2/ በዛ በሠርግ ቤት
ተገኝተሻል ድንግል ክልጅሽ ጋራ
ተግኝተሃል ጌታ ከእናትህ ጋራ
አዝ------------------//
እድምተኞች ሞልተው ከተጋበዙበት
ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ እልቆበት
ድንግል እናታችን ቤዛዊተ ዓለም
አንቺ ደረሽለት ሆንሽው አማላጅ
አዝ------------------//
አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው
ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላችው
ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ
ጌታን ያሳሰብሽው እመቤታችን ነሽ
አዝ------------------//
የጌታ አምላክነት የተገለፀበት
ምነኛ ታደለ የእነ ዶኪማስ ቤት
ዛሬም ይኸው በዚህ በሠርገኞች ቤት
በረከት ፈሰሰ በአምላክ ቸርነት
አዝ------------------//
ውኃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሲሆን
በቃና ገሊላ ሁላችን አየን
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን
ሁሌ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን
Download
በOct 03, 2024 ተጭኗል