እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

የእግዚአብሔር መልዓክ

የእግዚአብሔር መልዓክ

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
ለሶርያው ሰው ለማኑሄ እንደነገረው
በመሰዊያው ነበልባሉ ውስጥ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

ከዳን ወገን የሆነ በእግዚአብሔር ያመነ
ማኑሄ የሚባል ሰው የጌታ መላዕክ ታየው
ሚስቱ መካን ነበረች ልጅንም ያልወለደች
ሚካኤል ተገልጦላት በዘር ፍሬ ባረካት

የእግዚአብሔር  መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦፍራ አድባር ለጌድዬን የተገለጠው
እስራኤልን ከምድር ረሀብ ታደገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

አንተ ጽኑ ሃያል ሰው እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው
ክንድህን ላበረታ ተልኪያለው ከጌታ
አይዞህ ጌድዮን ያለው ቁርባኑን ያሸተተው
ከኛ ጋር ነው ሚካኤል ሰልፋችንን ይመራል

የእግዚአብሔር  መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦርና አውድማ ሰይፍን ይዞ ቆሞ የታየው
ዳዊት በመንቀጥቀጥ ፊቱን ፈለገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

በሦስት ቀን ቸነፈር እንዳትጠፋ ምድር
70ሺ ሰዎች ወድቀው መላዕኩ በቃህ አለው
ለምህረት ይመጣሉ ለመአት ይላካሉ
ሰይፉን በአፎቱ ከድኗል ሚካኤል ለህዝቡ ቆሟል

የእግዚአብሔር  መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
ስምኦን ጴጥሮስን ከወይኒ ቤት ገብቶ ያወጣው
የእጆቹን ሰንሰለት ፈቶ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

ከጠባቂዎች መሃል ኬፋን ከእንቅልፉ አንቅቷል
የተዘጋውን ደጃፍ አልተሳነውም ማለፍ
ሚካኤል እየመራው ጰጥሮስ እግሩ የቀናው
አውቆታል ልቡ በርቶ ዘለለ ስሙን ጠርቶ

Download

በOct 05, 2024 ተጭኗል