እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ሚካኤል ስለው 

ሚካኤል ስለው 

ሚካኤል  ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሀን በላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍፁም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያፅናናኝ / 2/

ከአለቆች ጋራ ህዝቡን የመራ
የሚመላለስ በዚያ ተራራ
ባህሩም ሸሸ ከማደሪያው
የጌታ መልዓክ ሲያናውጠው
ዘንዶውን አሸንፏል
ስሙን በክብር ፅፏል /2/

    አዝ=====

ከባዱን ጋራ ሚዳ ሆኖኛል
የወይኒው መዝጊያ ተከፍቶልኛል
አልናወጥም ከቶም አልፈራም
የጌታ መልአክ ነው ከእኔ ጋራ
ዘንዶውን አሸንፏል
ስሙን በክብር ፅፏል / 2/

   አዝ=====

ትቢተኛውን አሸንፎታል
ዳቢሎስ አሁን ዝናሩን ፈቷል
ታላቅ ፀጥታ በሰማይ ሆነ
እግዚአብሔር ብቻ ስሙ ገነነ
ዘንዶውን አሸንፏል
ስሙን በክብር ፅፏል /2/

    አዝ=====

ሚካኤል ሲቆም ፈጥኖ ደራሽ
የሚቃወሙኝ አጥብቀው ሸሹ
ታላቁ መልአክ  ከፊት ቀደመ
ታሪክ ተሰራ እንባችን ታበሰ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ፅፏል  /2/

Download

በOct 05, 2024 ተጭኗል