እንኳን ደህና መጡ
ግባ
የስሙ ትርጓሜ
የስሙ ትርጓሜ
የስሙ ትርጓሜ ማን እንደ እግዚአብሔር ነው
የሰውን ወደ አምላክ የአምላክን ወደ ሰው
እኛን የሚረዳን ዘወትር በምልጃው
የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው
ከጉድጓድ ተጥሎ ፍፁም ከሚያስፈራው
ከተራቡ አናብስት ዳንኤልን ያዳንከው
እኛንም ተራዳን ቸል አትበለን
ሰይጣን በተንኮሉ ወጥመድ ሳይጥለን
አዝ=====
የክፉ ሰው ስራው ክፉ ሃሳብ ነውና
በቅንነት መንገድ ከቶ አይሄድምና
የሞቱን ደብዳቤ ለባህራን ሲሰጠው
ሚካኤል አጥፍቶ በደስታ ለወጠው
አዝ=====
ገና ብላቴና ሳለው አንድ ፍሬ
ሰው ሁሉ ሲንቀኝ ምስጋናን ጀምሬ
ጸጋዬን አብዝቶ ያበቃኝ ለዚህ ክብር
የሚካኤል አምላክ ይመስገን እግዚአብሔር
Download
በOct 05, 2024 ተጭኗል