እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ኦ ሚካኤል

ኦ ሚካኤል

ኦ ሚካኤል/2/ ሊቀ መላዕክት
በኃጢአት እንዳንወድቅ እንዳንሞት
ፈጥነህ ተራዳን አጽናን በእውነት

ለያዕቆብ ነገድ - - - - - ሚካኤል
ለእስራኤል - - - - - ሚካኤል
ጠባቂያቸው ነህ - - - - - ሚካኤል
መልዓከ ኃይል - - - - - ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምሕረት
ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት/2/

    አዝ=====

ነጸብራቃዊ - - - - - ሚካኤል
ተክህኖ ልብስ - - - - - ሚካኤል
ሐመልማለ ወርቅ - - - - - ሚካኤል
ዓይኑ ዘርግብ - - - - - ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምሕረት
ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት/2/

    አዝ=====

በስዕልህ ፊት - - - - - ሚካኤል
እሰግዳለሁ - - - - - ሚካኤል
ፈጥነህ አነጋግረኝ - - - - - ሚካኤል
አለሁ በለኝ - - - - - ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምሕረት
ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት/2/

    አዝ=====

በክንፍህ ጥላ - - - - - ሚካኤል
ተከልለናል - - - - - ሚካኤል
ቅዱስ ሚካኤል - - - - - ሚካኤል
ክፉን አልፈናል - - - - - ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምሕረት
ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት/2/

    አዝ=====

ቅሩበ እግዚአብሔር - - - - - ሚካኤል
ታማኝ ባለሟል - - - - - ሚካኤል
ደራሽ ሲጠሩህ - - - - - ሚካኤል
ለታመኑህ ኃይል - - - - - ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምሕረት
ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት/2/




Download

በOct 05, 2024 ተጭኗል