እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ምድር አበራች

ምድር አበራች

ከመልአኩ ክብር የተነሳ ምድር አበራች/2/
ፀጋውና ክብሩ ሆኗት የምስራች
ሃያል/2/ ከመላእክት ክብሩ የገነነ
ሊረዳኝ የመጣው ቅዱስ ሚካኤል ነው
 
ሲደግፈኝ ክንዱ በዘመኔ
ምልጃው ሲጠብቀኝ እያለፈ ቀኔ
እየመራኝ በብርሃኑ ፋና
ሚካኤል መንገዴን አቀና
   ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
   ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
   ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
   እግዚአብሔር አየን በምሕረቱ

    አዝ=====
  
እያጽናናኝ ፍጹም ከድካሜ
ስጠራው ተፈወስኩ ዳንኩኝ ከህመሜ
ሊመግበኝ ለተራብኩት መና
ደረሰልኝ ሚካኤል ገናና
    ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
    ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
    ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
    እግዚአብሔር አየን በምሕረቱ

    አዝ=====
  
ያሻገረኝ መልአክ ሚካኤል ነው
በምልጃው ይደርሳል ቀርቦ ለለመነው
ለነፍሴ ከለላ ሆኖላት
አተረፈኝ ከዕደ ረበናት
      ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
      ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
      ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
      እግዚአብሔር አየን በምህሕረቱ
        





Download

በOct 07, 2024 ተጭኗል