እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ሚካኤል ስዩም
ሚካኤል ስዩም
ሚካኤል ስዩም (2)ሊቀ መላእክት መዝገበ ርራሄ(3)ወየዋህ
የደሀ አደጉን ልጅ ስለተቀበልከኝ
በአውደ ምህረትህ በፍቅር አሳደከኝ
ከመቅደስ ተክለህ መገብከኝ ህይወት
አዘጋጅተኸኛል ለሰማይ መንግስትህ
አዝ=====
በከንቱ እንዳልደክም ነብሴ እንዳትዝል
ትመግበኝ ነበር የህወትን ቃል
ወጣሁኝ ከአለም ተሰሎንቄን ረሣሁ
መጠማቴ ቀረ የህይወት ውሀ ጠጣሁ
አዝ=====
መዳንን እንድወርስ ሞትን እንዳላይ
ትረዳኝ ነበረ ከኔ ሣትለይ
በመንገዴ ሁሉ ከፊቴ ቀደምክ
አማኑኤል ብዬ ጌታን እንዳመልክ
አዝ=====
ምልጃህን ታምኜ ስኖር በመቅደስህ
ታሻግረኝ ነበር እጆቼን ይዘህ
በጎልማሣ ነቴ ነህና ከጎኔ
ጉልበቴም አንተው ነህ በእርጅና ዘመኔ
Download
በOct 07, 2024 ተጭኗል