እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ፈጥኖ ደረሰልኝ

ፈጥኖ ደረሰልኝ



ቅዱስ ሚካኤል  ፈጥኖ ደረሰልኝ
ኦ ከሳሼን ረግጦ አዋረደልኝ
ክንፉን ቅጥር አድርጎ ዙራዬ ሰፈረ 
የጠላቴን ምክር ወጥመድ ሰባበረx2

ሌጊዮን መከረኝ የሀሰትን ምክር
ሊያሳየኝ ፈልጎ የሙሴን መቃብር
አይጠቅመኝምእና  ሰወረው ሚካኤል
አፍሮ ተመልሷል ተዋርዶ ሳጥናኤል

    አዝ=====

ፅድቅን አስተማረኝ ሀጥያቴን ሳበዛ
ነፍሴ እንዳትኮነን በበደል ተይዛ
ወደ ሂወት መንገድ ይዞ እየመራኝ
የመዳኔን እራስ ጌታን አሳየኝ

    አዝ=====

ከታናሽነቴ ተግቶ የጠበቀኝ
ካጋንት አሰራር ምልጃው የታደገኝ
ዛሬም አለ ጎኔ በጎልማሳነቴ
የልቤ ብርሀነው  ሚካኤል አባቴx2

አዝ=====

ፀጋዬ እዳይጎድል በለአብ እንዳይረግመኝ
ተራዳዊዉ መላክ ከፊቴ ቁምልኝ
ባህያ አንደበት ነብዩን ገሰፀው
እብደቱን አግዶ ከመገድ መለሰው

Download

በOct 08, 2024 ተጭኗል