እንኳን ደህና መጡ
ግባ
የአፎምያ እረዳት
የአፎምያ እረዳት
የአፎምያ እረዳት ነህ ሚካኤል/2/
ቅሩበ እግዚአብሔር የልዑል
ፈጥነህ ድረስልን ስንጠራህ ሚካኤል
ፊት ለፊታችን አምላክ ሠደደህ
አቀናህልን መንገዱን ጠርገህ
የቤንሆርን ምክር አፈረስክ
ከልጆችህ ጋር ከነዐን ደረስክ
ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን
እንጠራሀለን ሚካኤል ብለን
አዝ=====
በቃዲስ ክንፍህ ተዘርግቶልን
ደመናው በአንተ ተጋረደልን
አብረኸን ልትሆን ጌታ የላከህ
አንተ ሚካኤል ታዳጊያችን ነህ
ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን
እንጠራሀለን ሚካኤል ብለን
አዝ=====
ሙሴ ሲለየን ደጉ አባታችን
ሚካኤል ነበር ከላይ መሪያችን
የማንነቱ ጉዞ እስኪያበቃ
እጅግ እረዳን የኛ ጠበቃ
ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን
እንጠራሀለን ሚካኤል ብለን
አዝ=====
ሳጥናኤል መክሮን የሀሰት ምክር
ሊወስደን ሻተ ሙሴ መቃብር
ስለማይጠቅመን አንተ ሠወርከው
ምክሩን በታትነህ አስጎነበስከው
ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን
እንጠራሀለን ሚካኤል ብለን
Download
በOct 10, 2024 ተጭኗል