እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ለኔ ያደረገው ሚካኤል

ለኔ ያደረገው ሚካኤል


ለኔ ያደረገው ሚካኤል

ለኔ ያደረገው ሚካኤል ብዙ ነው /2/
ከእግዚአብሔር ተልኮ ድንቅ  አደረገልኝ
አፅናኝና እረዳት ሚካኤል ሆነልኝ

ታናሽ ብላቴና ስምክን የማይረሳ
ደግፈኝ ሚካኤል ስወድቅ እንድነሳ
ስምህን በልቤ ፅላት እፅፋለሁ
በክንፎችህ ጥላ ዛሬም ድረስ እላለሁ

አዝ=====

ውለታህ እንዳይጠፉ ሁሌም ከሀሳቤ
ሚካኤል ሳልልህ ፍቅርህን ከልቤ
አንተነህ የዋህ መልአክት የእርግብ አምሳል
የብርሃን አክሊል ነህ ሚካኤል ኃያል

አዝ=====

ለኔ ያለህን ፍቅር በዓይኔ አይቻለሁ
ውለታህን ሳስብ እጅግ አደንቃለሁ
በነፍስም በስጋም መታመኛዬ
የምትጥብቀኝ መከታ ጋሻዬ

አዝ=====

ስወጣ ስገባ ከሌሎች እንቅፋት
ሚካኤል ጠብቀኝ ከሚገጥመኝ ጥፋት
ደግ ነው ሚካኤል ፍቅሩ በዝቶልኛል
በዘመኔ ሁሉ እሱ ይረዳኛል




Download

በOct 10, 2024 ተጭኗል