እንኳን ደህና መጡ
ግባ
የኃይላት አለቃ
የኃይላት አለቃ
የኃይላት አለቃ ሊቀ መላእክት
ሚካኤል ተዋጋ ወደቀ ጠላት
እግሬን በከፍታ በክብር እያቆመ
በዙሪያዬ ሠፍኖ ሠላሜን ከተመ
የፈሮን ህብሪት ንዶ
የቃዲስ ንዳድ ጋርዶ
ዛሬም ቢሆን ትላንትና
አውጥቶኛል ከፈተና
አዝ=====
ሰናክሬምን ተቃውሞ
ሠልፈኞቹን እረምርሞ
በጥሩ ልብ አራምዶኛል
በማደሪያው አፅንቶኛል
አዝ=====
በመንገዴ እየሄደ
ፃይረ ሞትን ያሣደደ
ወደጥልቁ ሣልጣል
በፅድቅ ያዘኝ ሚካኤል
አዝ=====
ስሙን ጠራው ከፍ አድርጌ
በክንፉ ስር ተሸሽጌ
መላከኃይል ቸር ወዳጄ
ሚካኤል ነው አማላጄ
Download
በOct 11, 2024 ተጭኗል