እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ከሚካኤል በቀር

ከሚካኤል በቀር




ከሚካኤል በቀር የሚያፅናናኝ የለም
እረዳቴ እርሱ ነው በመከራዬ ቀን/2/


ሀዘኔ እጅግ በዝቶ - - - ከሚካኤል በቀር
የሚረዳኝ ሳይኖር በስደቴ ዘመን
ሰላም ከእኔ እርቆ- - - ከሚካኤል በቀር
ጭንቀት አስቸገረኝ በዙሪያዬ ከቦኝ
ዛሬ ግን አፅናኜ - - - ከሚካኤል በቀር
ሚካኤል ደርሰ ጠላቴ አፈረልኝ
      ሚካኤል ነው - - - የዳዊት እረዳት ከጎሊያድ ያዳነው
       ሚካኤል ነው - - - መንፈሳዊ ብርታት ሀይልንም የሰጠው/2/

    አዝ=====

ቃልኪዳኑ ብሩህ - - - ከሚካኤል በቀር
ዝክሩን ለዘከሩት ስሙንም ለጠሩት
አጋንት አትቀርቡም - - - ከሚካኤል በቀር
ስእሉ ባለበት ድርሳኑን ቢደግሙት
በረከት ይገኛል - - - ከሚካኤል በቀር
በርሱ ቢማፀኑት ከለመኑት በእውነት
       ሚካኤል ነው - - - በትረ መስቀል ይዞ የሚጠብቀኝ
        ሚካኤል ነው - - - ከአንበሶች መንጋ የሚታደገኝ/2/

    አዝ=====

በኑሮአችን ሁሉ - - - ከሚካኤል በቀር
እርሱ ይመራናል ፈጥኖ ይረዳናል
ፈርኦንን ድል ነስቶ - - - ከሚካኤል በቀር
ከግብፅ አውጥቶናል በብርሃን መርቶናል
የኤርትራን ባህር - - - ከሚካኤል በቀር
ከፍሎ እንዳሻገረ ከነአን ደርሰናል
       ሚካኤል ነው - - - ከበልአም እርግማን እስራኤልን ያዳነ
       ሚካኤል ነው - - - ዛሬም በአዲስ ኪዳን ክብሩ የገነነ /፪/

Download

በOct 11, 2024 ተጭኗል