እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

​​በበረሃው በሃሩሩ

​​በበረሃው በሃሩሩ



በበረሃው በሃሩሩ
በሚያስፈራው በባሕሩ
እስራኤልን የታደገው
በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው

ሚካኤል ነው - - - - አፅናኝ ደጋፊዬ
ሚካኤል ነው - - - - በዱር በበረሃ
ሚካኤል ነው - - - - ነፍሴን ያረካልኝ
ሚካኤል ነው - - - - ከአለቱ ውሃ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሐ

አዝ=====

ሚካኤል ነው - - - - መብረቅ ያወረደው
ሚካኤል ነው - - - - ጠላት ድል የነሳው
ሚካኤል ነው - - - - የባህራን ወዳጅ
ሚካኤል ነው - - - - ሀዘኑን ያስረሳው
ቤቱን የሰራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደ አባት ደግሶ የዳረው

አዝ=====

ሚካኤል ነው - - - - ያሳደገኝ መልአክ
ሚካኤል ነው - - - - በፅድቅ የመራኝ
ሚካኤል ነው - - - - ስደክም ያገዘኝ
ሚካኤል ነው - - - - ስወድቅ ያነሳኝ
በችግሬ ሁሉ የቀደመልኝ
ሚካኤል እርሱ ነው ከጥልቁ ያወጣኝ

አዝ=====

ሚካኤል ነው - - - - ክሴን ያስቀደደ
ሚካኤል ነው - - - - የበደሌን እዳ
ሚካኤል ነው - - - - በአማላጅነቱ
ሚካኤል ነው - - - - ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ጽፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ

Download

በOct 12, 2024 ተጭኗል