እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ከዓለም ባህር ውስጥ

ከዓለም ባህር ውስጥ



ከዓለም ባህር ውስጥ ነጥቀህ ያወጠኸኝ
አንተ ሚካኤል ነህ እኔም ባህራን ነኝ(×2)

በጉያዬ የያዝኩት አላማ እቅዴ
የት እንደሚወስደኝ የያዝኩት መንገዴ
እኔ አላውቀውም አንተ አንብብልኝ
ሞት ካገኘህበት እፍ ብለህ አጥፋልኝ
በክንፎችህ ብዕር እጣዬን ፃፍልኝ

  ከጭንቅ ከመከራ ፈጥነህ/ነጥቀህ/ ያወጣኸኝ
  አንተ ሚካኤል ነህ እኔ አፎምያ ነኝ(×2)

በሬን እያንኳኳ ሚካኤል ነኝ ያለው
ያ የሐሰት አባት መድረሻ የሌለው
አፎምያ ቢለኝ በሐሰት ምላሱ
ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ቁምልኝ ለመልሱ
አንተ ባለህበት መች ይገኝ እርሱ

  ከዓለም ባህር ውስጥ ነጥቀህ ያወጠኸኝ
  አንተ ሚካኤል ነህ እኔ እንደ ሙሴ ነኝ(×2)

እናቴ ብትጥለኝ ወደ ወንዝ ፈርታ
ፈርኦን ሳይገለኝ ብለህ ሙሴ በርታ
መንገድና ምሥጢር አላውቅ ብል ለአምላኬ
ፍራቻ ቢይዘኝ ለሕዝቡ መላኬ
አንተ ነህ የረዳኸኝ ጠባቂ መልአኬ

  በባዕዳን ሃገር ክብር ሞገስ የሆንከኝ
  አንተ ሚካኤል ነህ እኔ ዳንኤል ነኝ(×2)

በአናብስቱ ጉድጓድ ቢጥሉኝ በግፍ
ደርሰሃል ሚካኤል ረበ በአክናፍ
ድንቅም ሰራህልኝ ንጉሱ እስኪገረም
እንዳንተ ሚካኤል የሚያፅናናኝ የለም/(×2)

  ከዓለም ባህር ውስጥ ነጥቀህ ያወጠኸኝ
  አንተ ሚካኤል ነህ እኔም ባህራን ነኝ
  በባዕዳን ሃገር ክብር ሞገስ የሆንከኝ
  አንተ ሚካኤል ነህ እኔ ዳንኤል ነኝ


Download

በOct 16, 2024 ተጭኗል